Seattle Public Schools

Resources

Discrimination Complaint

መድልዎ አልባ መግለጫ
እና የመድልዎ የአቤቱታ አቀራረብ ሂደት

ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች፣እኩል የትምህርት እድሎች እና እኩል የቅጥር ዕድሎች ያቀርባል። በማንኛውም መርሃ ግብሮች ወይም እንቅስቃሴዎች ውስጥ ፆታ፣ዘር፤ እምነት፣ቀለም፤ ሃይማኖት፤ ዝርያ ፣የትውልድ ቦታ፤ ዕድሜ፤ የኢኮኖሚ ሁኔታ፤ ጾታዊ አመለካከት፣ የፆታ ግንዛቤ ወይም ማንነትን ጨምሮ፣ እርግዝና፤ የጋብቻ ሁኔታ፤ አካላዊ ቅርፅ፤ ማንኛውንም የስነልቦና፣ የአዕምሮ ወይም የአካል ጉዳት፤ በክብር የተሰናበቱ ወታደር ወይም የውትድርና ሁኔታ፤ ወይም የሠለጠነ ውሻ መመሪያ ወይም የአገልግሎት እንስሳት መጠቀም መሰረት በማድረግ አድልዎ አይፈፅምም። ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ለ ቦይ ስካውትስ እና ለሌሎች የወጣቶች ቡድኖች እኩል እድል ይሰጣል::

መድልዎ ምንድን ነው?

መድልዎ የአንድ ግለሰብ ወይም ቡድን ህገ ወጥ የሆነ አያያዝ ነው። ምክንያቱም ግለሰቡ ወይም ቡድኑ የተወሰነ የቡድን አካል ስለሆኑ ናቸው።ይህ ቡድን የተጠበቀ(protected) ቡድን ተብሎ ይጠራል ። መድልዎ አንድን ሰው በተለየ መልኩ መያዝ ፣ወይም አንድን ሰው ፕሮግራም፣ አገልግሎት ወይም እንቅስቃሴን እንዳያገኝ መከልከል ወይም የአካል ጉዳተኝነትን ማስተናገድ አለመቻል ሊያካትት ይችላል።የመድልዎ ትንኮሳ በተጠበቀ ቡድን ውስጥ ያለው የአንድን ሰው አባልነት በመመስረት የቃል ወይም አካላዊ ትንኮሳ ሊሆን ይችላል።

የተጠበቀ(protected) ቡድን ማለት ምን ማለት ነው?

የተጠበቀ ቡድን ማለት ተመሳሳይ ባህሪያት የሚጋሩ እና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በአካባቢ ህጎች ላይ ከመድልዎ እና ከጥቃቶች የተጠበቁ የሰዎች ስብስብ ነው። በሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ውስጥ የተጠበቁ ክፍሎች ከላይ በመድልዎ አልባ መግለጫ ውስጥ የተገለፁ ቡድኖች እንደ ፆታ፣ ዘር፣ ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው ።

ስለ መድልዎ አቤቱታ እንዴት ማስገባት እችላለሁ?

ትምህርት ቤት ዲስትሪክቱ ውስጥ የሆነ ሰው በትምህርት ቤት ወይም በሥራ አካባቢ ውስጥ መድልዎ ወይ የመድልዎ ጥቃት ደርሶበታል ብለው ካመኑ፣መደበኛ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለዎት። የትምህርት ድስትሪክቱ የመድልዎ አልባ የአቤቱታሂደትሙሉውምቅጂለማግኘትወደየተማሪሰብአዊመብትቢሮበ OSCR@ristorantepizzerialaruota.com

አቤቱታ ከማስገባትዎ በፊት፣ ስለሚያሳስቡዎት ጉዳዮች ከት/ቤት ርእሰመምህር ጋር፤ ከሥራ ተቆጣጣሪ ጋር ወይም ከሲያትል የህዝብ ትምህርትቶች የእንባ ጠባቂ ጋር በ Ombudsman@ristorantepizzerialaruota.com ለመወያየት ይፈልጉ ይሆናል።

የአድልዎ መደበኛ ቅሬታ ፋይል ለማድረግ:
ለተማሪዎች፣ ለወላጆች/ለተንከባካቢዎች፣ እና ለህዝብ አባሎች፣ የተማሪ የዜጎች መብቶች ቢሮ (OSCR) በሲያትል

የህዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መድልዎ ስለመፈጸሙ ጥያቄዎችና አቤቱታዎች ለማስተናገድ ተብሎ የተሰየመ ነው:: የ OSCR አባል ለማነጋገር ወደ 206-252-0306 ይደውሉ ; ወደ OSCR@ristorantepizzerialaruota.com ኢሜይል ይላኩ; ወይም ወደ Seattle Public Schools, MS 32-149, P.O. Box 34165, Seattle, WA 98124-1166 ፖስታ ይላኩ። በተማሪ የዜጎች መብቶች ቢሮ ውስጥ፣ የሚከተሉት ሰራተኞች የተወሰኑ የመድልዎ ቅሬታዎችን ያስተናግዳሉ:

  • ለጾታ መድልዎ ወይም ፆታዊ ትንኮሳ የሚያሳስቡ ጉዳዮች ፣ የታይትል IX ባለሞያ በ 206-252-0367 ወይም በ Title.IX@ristorantepizzerialaruota.com ይገናኙ::
  • ለአካል ጉዳት መድልዎ የሚያሳስቡ ጉዳዮች ፣ የ504/ADA ቅሬታ አስተባባሪ በ 206-252-0306 ወይም በ OSCR@ristorantepizzerialaruota.com ይገናኙ::

ከአካል ጉዳት የተያያዙ ማስተካከያዎች እና/ወይም የቅጥር መድልዎ አቤቱታዎች፣ ፆታዊ ትንኮሳን ጨምሮ በሰራተኞች በኩል የሚነሳ ቅሬታ፣ የሰው ኃይል አስተዳደር ኃላፊ በ 206-252-0024 ወይም በ HREEOC@ristorantepizzerialaruota.com ወይም በ Seattle Public Schools, MS 33-157, P.O. Box 34165, Seattle, WA 98124- 1166 ይገናኙ።

የሲያትል የህዝብ ት / ቤቶች የመድልዎ የአቤቱታ አቀራረብ ሂደት

ደረጃ 1: ወደ የትምህርት ዲስትሪክት አቤቱታ ማቅረብ

በአብዛኛው ሁኔታዎች፣ ፍፃሜው ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ አቤቱታዎች በአንድ አመት ውስጥ መቅረብ አለባቸው። አቤቱታ በጽሁፍ መሆን፣ ምን እንደተፈጠረ መግለፅ፣ እና መድልዎ ነው ብለው ያመኑበትን ምክንያት መግለጽ አለበት። አቤቱታዎችን በፖስታ፣ በኢሜል፣ ወይም በእጅ ወደ የት /ቤት አስተዳዳሪ፣ ሥራ አስፈፃሚ፣ የተማሪ የዜጎች መብቶች ጽ/ ቤት፣ ወይም ሰብአዊ ሀብት ሊቀርቡ ይችላሉ።

የትምህርት ድስትሪክት የእርስዎ የጽሑፍ አቤቱታ ሲደርሰው፣ የዲስትሪክቱ የቅሬታ አቤቱታ አሰራር ሂደት ቅጂ ይሰጦታል። የተማሪው የዜጎች መብቶች ወይም የሰው ሀብቶች ጽ/ቤት የትምህርት ቤት ዲስትሪክቱ አቤቱታውን ለመፍታት እርምጃ መውሰዱን ያረጋግጣል፣ ይህም ፈጣን እና ጥልቅ ምርመራን ሊያካትት ይችላል። እንዲሁም ቅሬታዎ ያለ ምርመራ በአማራጭ የግጭት አፈታት ሂደት፣ ለምሳሌ እንደ ሽምግልና በመጠቀም ለመቅረፍ መስማማት ይችላሉ።

በተለየ ቀን ካልተስማሙ ወይም ከአቤቱታ ጋር የተያያዙ ልዩ ሁኔታ የጊዜ ገደብ እንዲራዘም ካልተፈለገ በስተቀር የትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት አቤቱታዎ ከተቀበለ በ 30 ቀን ውስጥ በፅሁፍ ምላሽ መሰጠት አለበት። የአቤቱታ ማስተካከያ ውሳኔ ከ 30 ቀናት በላይ የሚወስድ ከሆነ፣ የተራዘመበትን ምክንያት እና የሚጠበቀው የምላሽ ቀን በጽሁፍ ይነግርዎታል።

የትምህርት ቤት ዲስትሪክት ለአቤቱታዎ ምላሽ ሲሰጥ፣ ከሚከተሉትን የወሰነውን ውሳኔ በግልፅ ማስቀመጥ አለበት:

  1. በአቤቱታው ውስጥ የተካተቱትን ክሶች ውድቅ ማድረግ፣ወይም
  2. ክሶችን ማረጋገጥ እና የማረሚያ እርምጃዎችን ዝርዝር::

በተጨማሪም፣የትምህርት ቤት ዲስትሪክት አቤቱታው ውድቅ ካደረገው ፣ የት እና ማንጋ ይግባኝ እንደሚባል ጨምሮ ይግባኝ የማለት መብትዎ ማስታወቅያ የያዘ ይሆናል። 

ደረጃ 2: ወደ የትምህርት ቤቶች የበላይ ሃላፊ ይግባኝ ማለት

የትምህርት ቤት ዲስትሪክቱ ክሱን ውድቅ የማድረግ ውሳኔ ካልተስማሙ፣ ለት /ቤቱ ዋና ተቆጣጣሪ ይግባኝ ማቅረብ ይችላሉ።የትምህርት ቤት ዲስትሪክቱ ለአቤቱታዎ ምላሽ ከሰጥዎት በኋላ በ 10 ቀናት ውስጥ ለትምህርት ቤቱ የበላይ ሃላፊ በጽሑፍ ቅሬታዎ ማስገባት አለብዎ።

ይግባኙ በግዜው ሲደርስ፣የበላይ ሀላፊው ይግባኙን ለመገምገም ገለልተኛ የችሎት መርማሪ ይሾማል። ችሎቱ ቀጠሮ ይይዛል እና እርስዎ ከይግባኙ ጋር የተያያዙ ምስክሮች ወይም ሌሎች መረጃዎች ወደ ችሎቱ ሊያቀርቡ ይችላሉ።

ድስትሪክቱ የእርስዎ የይግባኝ ማሳወቂያ ከተቀበለ በኋላ በ 30 ቀናት ውስጥ የጽሑፍ ውሳኔ ይልክልዎታል። በጽሑፍ የቀረበው ውሳኔ ቅሬታዎ ለሕዝብ ትምህርት ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ ጽ/ቤት(OSPI ) እንዴት ማቅረብ እንደሚችሉ መረጃን ያካትታል።

ደረጃ 3: ቅሬታ ለ OSPI ማቅረብ

በትምህርት ድስትሪክቱ የይግባኝ ውሳኔ ካልተስማሙ፣ አቤቱታውን ለትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤት ማቅረብ ይችላሉ። የዲስትሪክቱን የይግባኝ ውሳኔ ከተቀበሉ በኋላ አቤቱታዎ በ 20 ቀናት ውስጥ ለ OSPI መቅረብ አለበት:: ቅሬታዎን ወደ OSPI በ ኢሜይል: Equity@k12.wa.us; በፋክስ: 360-664-2967; ወይም በፖስታ: OSPI Equity and Civil Rights Office, PO Box 47200, Olympia, WA 98504-7200 መላክ ይችላሉ።